
የዘር ፖለቲካ ከሕዝቡ መካከል ከወጣ በጣም ጠንካራ የሆነና ለመማርም ጊዜ የማይፈጅበት ሕዝብ ስላለን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ እንደምንችል አቶ ብርሃነ መዋ አስታወቁ።
አቶ ብርሃነ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፣ አገራችን ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም ያላት አገር ናት ። ሌሎቹ የእስያ አገራት እንዳደጉት ለማደጓ ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡ ጊዜ አይፈጅባትም። የዘር ፖለቲካ ከመካከሉ ከወጣ በጣም ጠንካራ የሆነ ሕዝብ ስላለን የኢኮኖሚ እድገት ይኖራል ብለዋል።
አገራችን በርካታ የተማረ የሰው ኃይል አላት ከዚህም በላይም በቀላሉ መማር የሚችሉ ሕዝቦች አሏት ያሉት አቶ ብርሃነ ፣ የተቀናጀ ሥራ ቢሰራ ለውጥ ምንም ያህል ጊዜ ሳይጠበቅ በአጭር ዓመት እንደሚመጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በቶሎ ለማደግ መለወጥ የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ ፣ እንዳለመታደል ሆኖ መልካም እሴቶቻችን እየተቀየሩ ነው ያሉት አቶ ብርሃነ ፣ ሰው ተዘቅዝቆ ሲሰቀል ሰው እንደተመልካች የሚያየበት፤ ሌላ አካባቢ ያሉ ችግሮች እዚህ ያለውን ሰው የማይሰማው ሆኗል ብለዋል።
በአሁን ወቅት ትግራይ ውስጥ ትልቅ ችግር መኖሩን ጠቅሰው፤ ይህንን ግን ሌላው ሕዝብ ጤናማ አድርጎ እያየው ነው ። አንድ ሕዝብ አንድ ሆኖ ካልጮኸ ችግሩ ዞሮ ራሱ ዘንድ ይመጣል። ይህ በፖሊሲም፤ በፖለቲካም፤ በኃይል እርምጃም ሊታይ እንደሚገባ አመልክተዋል። ምንጭ ኢፕድ