
ቡሩንዲን ሱዳንን ኡጋንዳን ኬንያን ጅቡቲን ከኪስዋ አስገብታ ኢትዮ ኤርትራ ላይ ግንባር አስፈጠረች ጅቡቲም የጦር ሰፈር በቅርቡ ሀገርዋን ለጎበኘው ለመጀመሪያው የግብፅ መሪ ኤል ሲሲ አከራየች ይላል ነጋሽ መሀመድ ያልነገረን ቢኖር ጅቡቲ የጦር ሰፈር ያከራያቸው ብዙሀገሮች መኖራቸዉን ነው። የገቢ ምንጭ ነው። የከፈለ ሁሉ ያገኛል።
ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የነጋሽ መሀመድ የአፍሪካ ተንታኝ ደንበኛው ኢትዮጵያ የጎረቤት ወዳጅ የላትም ከኤርትራና ሶማሌ ዉጭ ሲል ሰምተነዋል ሰሞኑን። ግብፅና ሱዳን በተለይ ወያኔ ባለፈው ኅዳር ጦርነት ከፍቶ ድባቅ ከተመታ በኋላ ሱዳን የምዕራብ ድንበራችንን ግብፅ በቤኒሻንጉል ታጣቂዎች በመሣሪያ ገንዘብ በማሰማራት በመተከል ብዙ ህይወት እንዳስጠፉ ብሎም ኅዳሤዉን ግድብ ሥራ ለማሰናከል ብዙ ሰርተዋል። ይህን የግብፅ ሴራ ነጋሽ መሀመድ አያዉቅ ይሆን ?? ይህንንስ ግብፅ ኪስዋ አስገባቸው ያላቸው አፍሪካዉያን አያዉቁ ይሆን
ነጋሽ መሀመድ የግብፅ ሚዲያ በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጨዉን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለምንከታተል እርሱ የዘረዘራቸው ጥቁር የአፍሪካ ሀገራት ይህን እያወቁ ከግብፅ ጋር ቆመውኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ ተፅዕኖ ያመጣሉ ማለት እንደ ግብፆች አፍሪካን መናቅ ይሆናል።
የአሜሪካ መንግሥት ያው እንደ ትራምፕ የት ነበራችሁግድቡ ሲጀመር ባይልም ግብፅን ለፓለስታይንና እስራኤል ጉዳያቸው አስፈፃሚነት ስለምትፈለግ ኅዳሤ ግድቡ ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እንዲወጣ ለማድረግ ያደረጉት ተፅዕኖ አልሰራም።
የኤርትራና የአማራ ጦር ከትግራይ ስላልወጣ በአሜሪካ የተጣለው የጉዞ ማዕቀብ ኢትዮጵያ በኅዳሤ ግድቡ ላይ ለግብፅና ሱዳን “የታሪካዊ ድርሻ” ዉሀ መጠን ፈርሙ የሚለዉን ባለመጨመሩ የዐረብ ሚዲያዎች አብደዋል እንደ ግብፅ ሱዳን ባወስልጣናት።
ግብፅ ከአሜሪካ ዉለታ ጠብቃ ነበር የአስራ አንዱ ቀን የሰሞኑ ዕስራኤልና ሀማስ ጦርነት እንዲያቆም በማድረግዋ። የግብፅ ዲፕሎማሲ የኪራይ ዲፕሎማሲ ነው አፍሪካዉያን ያዉቃሉ ከሱዳን በቀር። ነጋሽ መሀመድ የዚህ አወዳሽ መሆኑ ይገርም ይሆን ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ ??
በዛሬው ቀን የተጠናቀቀው የግብፅ ሱዳን የጦር ልምምድም የህዳሴ ግድቡን ስራ ለአንድ ቀንም አላቆመዉም። አዲሱ የግብፅ ጦር ሠፈር ጅቡቲና ግብፅ ልምምድ ያደርጉ ይሆን ኬንያን ጨምረው ?? የዲፕሎማሲ ምጥቀት እንደ ነጋሽ መሀመድ ??
ነጋሽ መሀመድ የግብፆችን የዲፕሎማሲ ታላቅነት ሲያወድስ የዘነጋው ዋናው ቁም ነገር የአል ሲሲ የቀይ መስመር የተሰመረበትን ቦታ አለመናገሩ ነው። የት ነው ይህ ቀይ መስመር የግብፅ ሚዲያ የዘወትር ጥያቄ ??
የኢትዮጵያ ህዝብ በአሜሪካ የተደገፈው የሲያድ ባሬ ወረራን በ ዘመነ ደርግ ያሸነፈው ኢትዮጵያን አናስደፍርም ብሎ መነቃነቁ ሲሆን የዛሬ 20 አመት አፍጋኒስታን የገባው የአሜሪካ ና የ ናቶ ጦርም መሸነፉን ለማመን የወሰደበት 20 ዐመት መሆኑ ነው ልዩነቱ። ግብፆች ነጋ ጠባ አሜሪኪያ ለሚሉት ትምህርት ይሆን ??
የግብፅ የአሜሪካ ተላላኪ ገዢዎች እጃችሁን አንሱ ኅዳሤ ግድቡ የኔ ነው የተቃዉሞ ሠልፍ ከግብፅ ገዢዎች አስተያየት ከመጠበቅ የአል ሲሲን ቀይ መስመር መፈለግ ይቀላል። ዉሸትና ጉራ የግብፅ ዲፕሎማሲ መመሪያ መሆኑን መላው ዐረብ ያዉቀዋል።
በአጠቃላይ ምሥራቅ አፍሪካም ሆነ አፍሪቃ በአጠቃላይ የአፍሪካ ችግር በአፍሪካዉያን ብቻ የሚፈታ እንጅ በግብፅ የአሜሪካና አዉሮፓ ተላላኪ ና በነጮች ና ዐረቦች አለመሆኑ ይሰመርበት።
የግብፅ የፀረ ኢትዮጵያ ሃምሳ ዐመት በላይ ያስቆጠረዉ አማፂያንን በማስታጠቅ መቶ ሺዎች እንዲገደሉ ሀብት እንዺጠፋ በኤርትራ ምስራቅ ኢትዮጵያ የፈፀመችዉ ወንጀል ዐባይን ለመቆጣጠር ሲያስችላት ዛሬ ኤርትራና ሶማሊያ የኢትዮጵያ አጋር ሆነው በራቸዉን ሲዘጉባት ኬንያ ጅቡቲ ቡሩንዲና ኡጋንዳ ኢትዮጵያ በኅዳሤ ግድቡ ላይ ከግብፅ ጎን ተሰለፉ ያለው ነጋሽ መሀመድ የአካባቢዉን ፖለቲካ በግብፆች መነፅር ከሚያዩት ከዐረብ ጋዜጠኞች ተርታ እንዲሰለፍ አድርጎታል። የኢትዮ ኤርትራ ትብብርን ሌሎች ምስራቅ አፍሪካዉያን የሚጠሉት አድርጎ ያቀረበው የነጋሽ መሀመድ ትንታኔ ግብፅ አወዳሽ የሆነ በዐረብ ሚዲያ ከምንሰማው የተለየ አይደለም። (ተድላ አስፋው)